በየዓመቱ የካቲት 29 የሚከበረውን ዓለማቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት በአዳማ ሂል ሆቴል መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡

በየዓመቱ የካቲት 29 የሚከበረውን ዓለማቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ
ኢንስቲትዩት በአዳማ ሂል ሆቴል መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ሴቶች፣ወጣቶችና ሕፃናት ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክተር ወ/ሪት ዘነበች ማሞ እንዳሉት ስርዓተ-ፆታ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል የሚመለከትና በጾታ መለያየት ያለውን በረከትና
ፀጋ በመረዳትና በመከባበር አንዳችን ሌላውን እንድንገነዘብ የሚረዳ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስርዓተ ጾታን በአግባቡ የተገነዘበ ማሕበረስብ
መብትና ግዴታውን ከማወቅ በዘለለ ከዚህ ቀደም የነበሩ መዛነፎች ያመጡትን ተጽዕኖ የማረም ተግባራትን ያከናውናል፤ ተጨማሪ ጉዳቶችም
እንዳይደርሱ ይከላከላል፡፡ ከዚህ አስተሳሰብ በመነሳትም የዘንድሮው የሴቶች ቀን ‘‘እኔ የእህቴ ጠባቂነኝ’’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል፡፡
በመቀጠል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱ
አባጊቤ እንዳሉት ሥርዓተ ጾታን መማርና ማወቅ ብቻውን ጠቃሚ አይደለም፡፡ ይልቁንም ለተግባራዊና ትርጉም ላለው ምላሽ መንቀሳቀስ
ያስፈልጋል፡፡ ሴት ልጅ ሁሉም ነገራችን ናት ካልን አለማጥቃትና ከጥቃት መከላከል የግድ ይላል እንዲሁም ጥቅማቸውን ከሚጎዱ አድሎዋዊ
አሰራሮችም መቆጠብ ይገባል፤ ‘‘እኔ የእህቴ ጠባቂነኝ’’ ካልን ሊታይና ሊጨበጥ በሚችል መልኩ መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በመቀጠል በትላልቅ ሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኢንስቲትዩቱ የጥራት ስራአስኪያጅ አቶ ፍቅረዓብ
ማርቆስ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት በአለማቀፍ ደረጃም ሆነ እንደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩ እንስቶችን
አንስተው ስላከናወኗቸው ተግባራት፣ ስለተጓዙበት መንገድና ውጣውረድ እንዲሁም ስለ ሕይወት ፍልስፍናቸውና መርሃቸው አንስተው አስተማሪነት
ያለው መረጃ ስጥተዋል፡፡ አዕምሯዊ ንቃት (Mind-set) እና አዕምሯዊ ብቃት (Emotional Intelligence) በሚሉ ርዕሰ
ጉዳዮችም ዙሪያ ሰፋ ያሉ ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን ተሳታፊዎችን በመልካም መንገድ ያነሳሳና ንቃትንም የሰጠ መሆኑ ተስተውሏል፡፡ በመድረኩ
ላይ የሴቶችን ጠንካራ ስብዕና የሚያወሱ ግጠሞችም ቀርበዋል፡፡
ዓለማቀፉ የሴቶች ቀን በዓለም ለ111ኛ እንዲሁም በአገራችን ደረጃ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ መከበሩ
የሚታወስ ነው፡፡
Comments(0)