ይከተሉን :
Contact Us
Customer Service
Service Request
Form
FAQs
Services
Calibration & Measurements
In house Service
On Site Services
Mobile Service
Scientific Equipments Maintenance
Medical Equipment
Nuclear Equipment
Electro Mechanical Equipment
Measurement & Analysis Equipment
Training & Consultancy Service
Medical Equipment training and consultancy
Nuclear Equipment training and consultancy
Electro Mechanical Equipment training and consultancy
Measurement & Analysis Equipment training and consultancy
Accreditation
Flexible Scope
Certification of competency
Metrology Laboratories
Mechanical Metrology Laboratories
Mass Laboratory
Volume Laboratory
Density Laboratory
Pressure Laboratory
Force Machines Calibration Laboratory
Torque Laboratory
Hardness calibration Laboratory
Temperature & Chemical Metrology Laboratories
Electrical Time & Frequency Metrology Laboratories
Radiation Metrology laboratory
Dimensional Metrology Laboratories
Publications
Gallery
Plan & Report
Research & Development
References
Announcement
News
Events
Vacancy
Tender
About Us
News
Home
News
የኢትዮጵያ ቤተ-ሙከራዎች ማህበር (ELA) ዳግም ምስረታ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሔደ፡፡
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የተለያዩ ውጣውረዶችን ሲያልፍ የቆየው የኢትዮጵያ ቤተ-ሙከራዎች ማህበር (ELA) የዳግም ምስረታ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ በጉባኤው መክፈቻ ላይ የማህበሩ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የሳይንሳዊ ሥነ-ልክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሠ ጌርጊሶ እና በኢትዮጵያ የጀርመኑ ሥነ-ልክ ተቋም(ፒቲቢ) ፕሮጅክት አስተባባሪ ሚስተር ኡኩሜ ኢኮን አርቺቦን የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ በወቅቱ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቤተሙከራዎች ማህበርን ተሞክሮ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጌታ ደርበው እንዳሉት ለፍተሻ፣ ለኢንስፔክሽን፣ ለቬሪፊኬሽን፣ ለምርምር እና ስርፀት፣ ለኢንዱስትሪዎች ቁጥጥር ላቦራቶሪዎች እንዲሁም ለአናሊሲስና ለመለኪያ መሳሪያዎች ወይም ለልኬትና እርከን ተዋረድ ትስስር እና ለጥገና አገልግሎቶች ብቃትና ተደራሽነት ማደግ ሁነኛ ሚና የሚኖረው የኢትዮጵያ ቤተ-ሙከራዎች ማህበር (ELA) መልሶ ማቋቋሚያ ጠቅላላ ጉባኤ በመካሄዱ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሙሉጌታ አክለው እንዳሉት የኢትዮጵያ ቤተ-ሙከራዎች ማሕበር ከተመሰረተ 2002 ዓ.ም ጀምሮ ባለፈባቸው ውጣውረዶች ውስጥ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ለረጅም ጊዜ ፕሬዚደንት ሆኖ ከመምራቱ በተጨማሪ ማሕበሩ ለሀገር ሊሰጥ የሚችለውን ወሳኝ ጠቀሜታ በቅጡ በመገንዘብ ከአጠቃላይ መዳከምና ብሎም መጥፋት ለመታደግ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የራሱን የማይጠፋ አሻራ ማኖሩን ገልፀዋል፡፡ ጠንካራ የጥራት መሰረተ ልማት በመገንባቱ ሂደት የማህበሩን ሚና በሚገባ በመረዳት ሚኒስትር መስሪያ ቤቶቻችን ላደረጉልን ድጋፍና ክትትልም ማመስገን ይገባል ሲሉ አስምረውበታል። መላው የማህበሩ መስራች አባላትም የሀገርን ገጽታ፣ የምርትና አገልግሎት ተዓማኒነት ሊገነባ ለሚችለው ማህበር ጠንክሮ መውጣት እያደረጉ ያለውን ጥረት አድንቀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ ቤተሙከራዎች ማህበር ህጋዊ ሰውነቱን በማግኘት ሂደት ባገጠሙት ተግዳሮቶች ተስፋ ባለመቁረጥ የጀርመን ሥነ-ልክ ተቋም (PTB) ከቀደመው የማህበሩ ምስረታ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በገንዘብና በቴክኒክ ረገድ ያደረገው ድጋፍ እውቅና የሚገባውና የሚመሰገን መሆኑን ጠቁመዋል። ማህበሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት እና PTBን ከማመስገናቸው በተጨማሪ የኢትዮጵ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ አክሬድቴሽን አገልግሎትም ተጋብዘው ለማህበሩ መጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ማስቻል እንደሚገባም ጠቁመዋል። የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ተጠሪ የሆኑባቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማህበሩን በልዩ ሁኔታ የሚደግፍበት አግባብም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት ያስፈልጋል።
Communication D
2 months ago
አራቱ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ያዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ፡
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) አራቱ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ያዘጋጁትና አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የተሳተፉበተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ሐሙስ ሕዳር 22 ቀን 2016ዓ.ም በጅማ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ግንዛቤ ማስጨበጫውን በንግግር የከፈቱት የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መዓዛ አበራ እንደተናገሩት የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት በአንድ የተሳተፉበት ፕሮግራም መዘጋጀቱ ሕብረተሰቡም ሆነ ደንበኞች የየተቋማቱን ኃላፊነትና ተግባር ልዩነት እንዲገነዘቡ እንዲሁም የትኞቹ ቦታዎች ላይ ደግሞ ተቋማቱ በጋራ እንደሚሰሩ መረጃ እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ተሳታፊዎች ለሚኖራቸው ሃሳብና ጥያቄ ከምንጩ ምላሽ የሚያገኙበትን ሁኔታም ያመቻቻል ብለዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ጨምርው እንዳሉት የጥራት ደረጃን ከፍ የማድረግ ፍላጎት ያለው መንግስት እስከ አስራ ሁለት የሚደርሱ ግዙፍ የሕንፃ ግንባታዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረው በዚህም ከፍተኛ የአገልግሎት ጥራትና ስፋት ለውጥ እንደሚኖር አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ከመክፈቻ ንግግሩ በማስቀጠል የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማቱ ተወካዮች ስለሚሰጧቸው አገልግሎቶችና ደረጃዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የአንድ ተጋባዥ ተቋም የሥራ ኃላፊም በምግብ ምንነትና ደህንነት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል፡፡ የኢትጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የሣይንሳዊ ሥነ-ልክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ጌርጊሶ እንደገለጹት ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት በካሊበሬሽን ዘርፍ ከስድስት በላይ ዓለማቀፍ እውቅና ያለውና በሌሎችም ዘርፎች ተጨማሪ እውቅና ለማግኘት እየሰራ ነው፡፡ በሣይን መሳሪያ ዘርፎችም በማማከር፣በሥልጠና፣በቴክኒክና ጥገና ዙሪያ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ጨምረው እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ በሌሎች ሀገሮች እንደሚሰራበት የጥናትና ምርምር ተግባራት ላይ በማተኮር አገልግሎቶችን ብቁ ለሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች የማስተላለፍ ዕቅድ ያለው ሲሆን ይህንንም ለማሳካት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የድርጅቶች ተወካዮችም በቀረቡት ሃሳቦችና በጥራት መሰረተልማት ተቋማት አገልግሎትና እንቅስቃሴ ዙሪያ ጥያቄ አቅርበው ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
Communication D
2 months ago
ኢንስቲትዩቱ 34ኛውን የዓለም ኤድስ ቀን አስቦ ዋለ፡
አዲስ አበባ፣ ህዳር 28/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት በዓለም ለ35ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ "የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ ኤችአይቪ መከላከል!" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የዓለም ኤድስ ቀን በፓናል ውይይት አስቦ ውሏል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ዘነበች ማሞ ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ቀኑ ማህበረሰቡ ኤችአይቪን በመከላል ረገድ የሚጫወተው የማይተካ ሚና በሀገር አቀፍ ደረጃና በማህበረሰብ አደረጃጀት ዕውቅና የሚሰጠው ዕለት ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ማህበረሰቡን በማብቃት ወደ መሪነት ደረጃ ለማምጣት እንዲሁም የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቃል የምንገባበት መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ በሌላ በኩል ዕለቱን በተመለከተ የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡት በለሚኩራ ክ/ከተማ ጤና ጣቢያ የጤና መኮንን የሆኑት ወ/ሮ ፋሲካ ስዩም እንደገለፁት እ.ኤ.አ በ2022 በዓለም አቀፍ ደረጃ 39 ሚሊዮን ሰዎች ኤችአይቪ በደማቸው እንደሚገኝ፣ ከ630 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን በኤድስ ምክንያት እንዳጡ በዚሁ ዓመት 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ አዲስ በኤችአይቪ እንደተያዙ ጠቁመዋል፡፡ እንደ ጤና መኮንኗ ማብራሪያ በሀገራችን ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል የኤችአይቪ ስርጭት ምጣኔ 0.91 በመቶ ሲሆን በዚህም ስሌት ከ610 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ፣ ከ8 ሺህ በላይ በዓመቱ ውስጥ አዲስ የተያዙ እና ከ11 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በኤድስ ምክንያት እንደሚሞቱ አስረድተዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ ፕሮግራሙን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት ስለ ኤችአይቪ መስማትና ማወቅ ከጀመርን ብዙ ጊዜ ብናስቆጥርም በሚፈለገው ልክ የባህሪ ለውጥ ማምጣት አልተቻለም፡፡ በፅሁፉ ላይ የተጠቀሱ አህዛዊ መረጃዎች ብዙ ነገር ስለሚናገሩ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ከሁላችን የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ እንደ አቶ ፍቅረአብ ገለፃ ተቋማችን የመስክ ስራ የሚበዛበት በመሆኑ የመጋለጥ ዕድላችንም በዚያው ልክ ሰፊ ስለሆነ እራሳችንን መግዛትና መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ "ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፤ማስተዋል ይጋርድሃል" የሚለውን ቃል ሁሌም ማስታወስ ለህይወታችን ይጠቅማል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Communication D
2 months ago
ኢንስቲትዩቱ 18ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል አከበረ፡
አዲስ አበባ፣ ህዳር 26/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከብሔራዊ የጥራት መሰረተ-ልማት ተቋማት ጋር በመሆን "ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል 18ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል አክብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ የጥራት መሰረተ-ልማት ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን፣ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እና ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
Communication D
2 months ago
‹
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
›