አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች "በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተመሰረተበትን 116ኛ ዓመት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረው ውለዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እንደገለፁት ቀደምት አባቶቻችን የህይወት ዋጋ ከፍለው ሀገራችንን በመጠበቅ ለእኛ አስረክበዋል፡፡ የዚህን ታላቅ የቅብብሎሽ አደራ ጠብቀን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ዶክተር ሙሉጌታ አክለውም ሠራዊቱ የህይወት መስዋዕትነት የሚከፍል ከሆነ እኛ ደግሞ ቀላል የሆነውን የእውቀትና የጊዜ መስዋዕትነት በመክፈል ሀገራችንን በልማት ማጎልበት ይኖርብናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ በሌላ በኩል ከመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የተላከን ሠነድ መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን ሰፊ ሀሳቦችም ተንሸራሽረውበታል፡፡
.
Comments(0)