የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ በድሬዳዋ ከተማ ግምገማ አካሂዷል፡፡ በግምገማው ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንደተናገሩት የዛሬው ፕሮግራም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የዕቅድ አፈፃፀማቸውንና የልምድ ልውውጦችን በየዓመቱ በዙር እንዲያካሂዱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተከናወነ መሆኑን ገልፀው ቀደም ሲል በደሴ ቅ/ጽ/ቤት እንደተደረገ አስታውሰዋል፡፡
.
Comments(0)